የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ዉሳኔና የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እርምጃ

57
3049

የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ሲያጠናቅቅ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑትን አቶ ለማ መገርሳን ከስራ አስፈፃሚ እና ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን የሚታወስ ነዉ፡፡ የፓርቲዉ ዉሳኔም በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ መደናገጥ በመፍጠሩ አንዳንድ አባላቱ ዉሳኔዉን በዝምታ እንደማይመለከቱትና የመፈንቅለ መንግስት ስጋትም እንዳለ እየተዘገበ ይገኛል፡፡ 

ገዢው ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋን እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንን ከፓርቲዉ ያገደ ሲሆን አባላቱን ያገደዉ ኃላፊነታችሁን በአግባብነት አልተወጣችሁም በሚል መሆኑም ታዉቋል። በ2011 ዓ/ም ኢንጂነር አይሻ ሙሀመድን በመተካት የኢፌድሪ የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ ትውልዳቸው በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ በአሁን አጠራር ሆሮ ጉዱሩ ውስጥ በምትገኝ ጉደያ ቢላ በምትባል ወረዳ ሲሆን፤  በተወለዱበት ምዕራብ ኦሮሚያ አከባቢ የቁጣ አመፅ ሊባባስ እንደሚችል ይገመታል።

አቶ ለማ መገርሳ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ፣ በፌደራል የኦሮሚያ ክልል የደህንነት ሃላፊ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ እንዲሁም ከ2008 ዓ.ም አዲስ ዓመት መጀመሪያ አንስቶ የኦህዴድ ሊቀ መንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጥ እያገለገሉ መሆናቸው ይታወሳል።   አቶ ለማ ቀደም ባሉት የሥራ ጊዜያቶች “ቲም ለማ” የሚባለውን ቡድን በመምራት ጉልህ ሚና የነበራችዉ ሲሆን ሁሉም የብሄር ፓርቲዎች ወደ አንድ ወጥ ፓርቲነት መቀየሩ እና የሀገሪቱ ገዢ ፓርቲ ወደ ብልፀግና ፓርቲ መቀየሩን እንደማይስማሙበት እና በጥድፍያ የተወሰነ ዉሳኔ መሆኑን በሚድያ ቀርበዉ ከተቃወሙ ብኋላ ከሚድያ ርቀዉ ነበር፡፡ አሁን በተከሰተው ደግሞ  ከፓለቲካ መድረክ መገለላቸው የማይቀር ነው፤ ምክንያቱም ጠ/ሚሩ የለማን አፍ የሚያሸብብ ፋይል ሳይዙ እንዲህ አይነት አወዛጋቢ እርምጃ አይወስዱም ነበር ሲሉ ተንታኞች ያስረዳሉ። 

57 COMMENTS

  1. Hi, I do think this is a great web site. I stumbledupon it
    😉 I may come back once again since i have saved as a favorite it.
    Money and freedom is the best way to change, may you be rich
    and continue to guide others.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here