እንድትፅፉ እናበረታታለን፤ እናስተናግዳለን!

በዚህ ዓምድ ፅሕፍዎ እንዲታትም/ፓስት እንዲደረግ የሚሹ ከሆነ ፅሑፉ የሚከተሉት እንዲያሟላ እንጠይቃለን

1.      ቢበዛ ከ2ሺ ቃላት በፍፁም መብለጥ የለበትም፤

2.     ግልፅና በአንድ አርእስት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፤

3.     እውነታንና መረጃ ያጣቀሰና ፤ በፍፁም ከአሉባለታና ከሰሚ ሰሚ የራቀ መሆን ይኖርበታል፤

4.     በተቻለ መጠን የሚከተሉት አንቀፆች/ክፍሎች ቢኖሩት ይመረጣል፤

a. መግቢያ አንቀፅ፤ አርእስቱን ማስተዋወቅ፤ ስለ ርእሰ ጉዳዩ ለመፃፍ የተጠቀሙበት ዘዴ፤ የርእሰ ጉዳዩ ዋና መልእክት።

b. ዝርዝር ጉዳዮች የያዝ አንቀፅ፤ ዋና ዋና ፍሬ ሃሳቦች፤ በርእሰ ጉዳዩ ያሉ የተለያዩ አመለካከቶች፤ በርእሰ ጉዳዩ ላይ በአስረጂነት የቀረቡ ሃስቦችና መከራከሪያዎች፤ የፀሓፊው አስተያየት ሚዛንና ምክንያታዊነት

c. ማጠቃለያ አንቀፅ፤ የፅሑፉ መነሻና መድረሻ ዋና ዋና መደምደሚያ ሓስቦች። ከአምዱ ዋና አላማ ጋር በማያያዝ የፅሁፉ አድማስ አንደምታ።

የላኩልን ፅሑፍ መመዘኛዎቹን አሟልቶ እንዳለ እንዲታተም (ፓስት) ከተወሰነ ለፀሓፊው በ2 ቀናት መልስ እንነግራለን። ፅሁፉ ከዝርዝር መመሪያዎች ወይ ከትሪቡኑ አላማ ውጭ ሆኖ ሲገኝ፤ ወይ ኢዲቶርያል ፓሊሲ ምክንያት ፓስት የማይደረግ ከሆነ ፤ በ3 ቀን ውስጥ ውሳኔችንን እንሳውቃለን። አንዳንድ ማስተካከያዎች ተደርገው ፅሁፉ መውጣት የሚችል ከሆነ፤ መስተካከል ያለባቸውን በመጠቆም በ 4 ቀናት ውስጥ መልስ እንሰጣለን።